From propaganda Unit Ts.M.B
ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ
በጀርመን ሀገር ለምትገኙ
ኢትዮጵያውያን በሙሉ
Aufruf zum großen Demonstrationszug
für allen in Deutschland
lebenden Äthiopien
በዘረኛው የወያኔ መንግሥት፣ በኢትዮጲያ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ፣ ጭቁን የሆነውን የኢትዮጲያ ህዝብ፣ በዘር ብጐሳና ብሃይማኖት በመከፋፈል፣ በኣሁኑ ሰዓት ሃገራችን በከፍተኛ ውድቀት ላይ ትገኛለች። ይህን ለመከላከልና ብሎም ለማዳን፣ ይህ ጕዳይ ያገባኛል የሚል ማንኛውም ኢትዮጲያዊ-ሁሉ፣ በኣንድነት ተነስቶ፣ ተቃውሞውን እንዲያሰማ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር (EPPF) ጥሪውን ያስተላልፋል።
የወያኔ መንግሥት በሰፊው የኢትዮጲያ ህዝብ የጫነው የባርነት ቀንበር እንዲቆም ዘንድ፣ ሁሉም ስለ ኢትዮጲያ ህዝብ ሰላምና ፍትሕ የሚቆረቆር "ዘብ ሊቆም" ይገባዋል በሚል መሪ-መፈከር በማንገብ፣
ቀን፣በ18 ጥቅምት 2005
"27. Oktober 2012"ቦታ፣ ኑርንበርግ ከተማ "Nürnberg"
ሰዓት፣ 12፣00 እስከ 16፣00መነሻ፣ ኣም ፒሌረር "Am Plärrer"
መድረሻ፣ ኣውስለንደር ኣምት "Aüsländeramt"
በማድረግ የህዝባችንን ጭቆና ለማሳወቅና፣ የስደተኛውን ችግር ለጀርመን ህዝብና መንግሥት ለመግለጽ፣ ለምናደርገው ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ማንኛውም ሃገር ወዳድ ኢትዮጲያዊ፣ ዘር፣ ፆታ፣ ሃይማኖት እንዲሁም የፖለቲካ ወይም የድርጅት ልዩነት ሳንለይ፣ በኣንድነት ስለ የወደፊት ኢትዮጲያ ልኡላዊነት በጋራ በመንቀሳቀስ የዜግነት ግደታችን እንወጣ
ማሳሰቢያ፦ "ጕልቻ ቢለዋወጥ ወጥ ኣያጣፍጥም!" እንደተባለው ሁሉ፣ የወያኔ-ኢህኣዲግ-ሥርዓት ከስር መሰረቱ እስካልተደመሰሰ ድረስ ሰላምና ዲሞክራሲ ይመጣል ብሎ ማሰብ "ከእባብ-እንቁላል የዶሮ ጫጩት ይፈለፈላል" ብሎ መጠበቅ ይሆናል።
ለበለጠ መረጃ፦ 0152-12102661 015210224716 015210249483 015210539047 015210249750
www.eppfguard.com Email kirarayiso@googlemail.com